ቀን 03/10/2013 ዓ.ም
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2013 ዓ.ም በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በክረምት መርሃ ግብር አመላካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመላካቾች ከሰኔ 03 እስከ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ድረስ ባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሪጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ትምህርት የሚሰጥባቸው መስኮች፡-
Faculty- Faculty of Chemical & Food Engineering
UG Programs
BSc in Applied Human Nutrition
MSc Programs
Food safety and Quality
Postharvest Engineering and Management Food Technology Process Engineering Environmental Engineering Sugar Technology Industrial Biotechnology Applied Human Nutrition |
Faculty- Faculty of Civil &Water Resource Engineering
UG Programs
BSc in Civil Engineering
BSc in Hydraulics and Water Resources Engineering BSc in Irrigation and Water Resources Engineering MSc Programs
Construction Management and Technology
Engineering Hydrology Hydraulic Engineering Water Supply & sanitary engineering Irrigation Engineering & Management |
Faculty- Faculty of Computing
UG Programs
BSc in Computer Science
BSc in Information Technology BED in Information Technology MSc Programs
Computer Science |
Faculty- Faculty of Mechanical & Industrial Engineering
UG Programs
BED in Engineering Drawing and Design
BSc in Electro-Mechanical Engineering Production Engineering and Management MSc Programs
Product Design and Development
Industrial Management Manufacturing Engineering Thermal Engineering Mechanical Design Engineering drawing and design Agricultural mechanization engineering Electromechanical engineering |
Bahir Dar Energy Center
MSc Programs
Sustainable Energy Engineering |
የመግቢያ መስፈርት፡-
ለሁለተኛ ዲግሪ፡-
- ከስልጠና መስኩ ጋር ተዛማች የሆነ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት
- የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል
ለመጀመሪያ ዲግሪ፡-
- የመሰናዶ ትምህርት ለጨረሱ፡- በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሰረት ወይም፤
- ከ1994 ዓ.ም በፊት ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ወይም፤
- ከ1994 ዓ.ም በፊት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም፤
- ከ1994 ዓ.ም በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ-4 ያጠናቀቁ እና የደረጃ-4 የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ
በድሮውም ሆነ በደረጃ-4 ዲፖሎማ ለምትመዘገቡ ኦፊሻል ትራንክሪፕት ከምዝገባ በፊት መድረስ አለበት፤
የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም፤
ለማመልከቻ ለBSc 100 ብር ለMSc 200 ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል፤
ለነባር የተቋሙ የክረምት ተማሪዎች፡- የመግቢያ ቀን ሐምሌ 4 እና 5 ሲሆን የ 2012 ዓ.ም የርቀት ኮርሶች ቱቶሪያል እና ፈተና የሚሰጠው ሐምሌ 7-11 መሆኑን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም በማታዉ መርሃግብር በምህንድስና የትምህርት ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በፍኖተ ሰላም መምህራን ኮሌጅ ለማስጀመር ዝግጅት ያጠናቀቅን ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በኮሌጁ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ከ07/10/2013 እስከ 21/10/2013 ዓ.ም. ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሪጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት