ክፍት የሃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
=================
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመካከለኛና ዝቅተኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት፣ ምደባ ለመደንገግ የሴኔት መመሪያ ቁጥር 05/2014 መስፈርት መነሻ በማድረግ ለመካከለኛና ዝቅተኛ የአካዳሚክ ኃላፊነት ቦታዎች ማወዳደሪያ መስፈርት አፅድቆ እየተገበረ ይገኛል። በዚህም መሰረት ለሳንስ እና ቅድመ ምህንድስና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ቦታ ለመወዳደር የምትፈልጉ መምህራን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርት እና የሥራ ልምዳችሁን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ከአምስት ገፅ ያልበለጠ ስልታዊ ዕቅድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅክ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት