
የሳንስ እና ቅድመ -ምህንድስና ማስተባበሪያ የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቀረበ
Campus Name
27 Apr, 2024
የሳንስ እና ቅድመ -ምህንድስና ማስተባበሪያ የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቀረበ
[ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር]
=========================
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ3 ተከታታይ ቀናት በጎንደር ከተማ ሲያካሂደው የነበረውን የሪፖርት ግምገማ መድረክ በትናንትናው ዕለት አጠናቅቋል፡፡ በመድረኩ ሁሉም ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና የማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊዎች የየክፍላቸውን አመታዊ የእቅድ ክንውን ሪፖርት በየተራ ያቀረቡ ሲሆን የሳንስ እና ቅድመ -ምህንድስና ማስተባበሪያም የ2014 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ መስፍን ሙሉ የጽ/ቤቱ አስተባባሪ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በወይይቱም በአመቱ ጽ/ቤቱ የታዩ ጠንካራ ልምዶችን በመቀመርና በክንውኑ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ትምህርት ወስዶ ስኬታማ ክንውን ለመፈጸም ወሳኝ ግብዓት እንደትገኘ ተገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻና የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት ያሳለፍነው የበጀት አመት እንደሃገርም እንደተቋምም ብዙ ፈተናወችና ውጣውረዶች የበዙበት ቢሆንም ሁሉም ክፍሎች ችግሮችን ተቋቁመው እቅዳቸውን ለማሳካት የሄዱበት ርቀት ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ገልጸው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አክለውም የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማ በክንውኑ የነበሩ ክፍተቶችን በጋራ የመለየትና ለቀጣይ የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ትምህርት ወስዶ ስኬታማ ክንውን ለመፈጸም በመሆኑከዚህ አኳያ መድረኩ ግቡን ያሳካ እንደነበር ገልጸዋል፡፡