ለቅድመ ምህንድስና ተማሪዎች የፕግራም ትውውቅ ተካሄደ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለቅድመ ምህንድስና (pre-engineering) ተማሪዎች የፕሮግራም (Department) ትውውቅ አካሄደ፡፡ተቋሙ በ 5ፋኩልቲዎች 16 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 27 ማስተርስና 11 የፒኤችዲ ፕሮግራሞች፤ 5220 ተማሪዎችን  በመደበኛው ፕሮግራም ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በእለቱ በተቋሙ የሚሰጡ የምህንድስና ትምህርት ፕግራሞች በተወካዮች አማካኝነት ለተማሪዎች ስለፕግራሞቹ ገለፃ አካሄደዋል፡፡ ፕሮግራሞች ምን አይነት ችሎታ(Skill) እንደሚፈልጉ፣ ምን ዓይነት የሥራ እድሎች እንዳላቸው እና  ቢመርጧቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች ለዚሁ ዓላማ በተቋማችን ባለምያዎች የበለፀገውን ሶፍትዌር በመጠቀም  እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ በባለምያዎች ማብራሪያ ተሠጥቷል፡፡

በመጨረሻም የተቋሙ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ዜናማርቆስ ባንቴ ለተማሪዎች መልእክት በማስተላለፍ እና ሶፍትዌሩን ያበለጸጉ መምህራንን በማመስገን ፕሮግራሙን ዘግተዋል፡፡

images: 
Share