ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና መውሰድ ይጠበቅባቸዋል

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በልዩ ልዩ የሙያ መመስኮች በብቃት የስለጠነ ሥራ መሪ ፣ ተመራማሪ፣ አዲስ ዕውቀት አፍላቂ ዜጋ ማፍራት ይችሉ ዘንድ ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ  መሆኑ ይታወቃል ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት በተለይም የምሩቃን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ምዘናዎችን መስጠት በተለይም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎችም በራስ መተማመንን እንዲያጎለብቱ ያደርጋል፡፡ ስለዚህም በዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን ትምህርት ተከታታለው ያጠናቀቁ የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ዕጩ ምሩቃን ከመመረቃቸው ቀድሞ አጠቃላይ ምዘና እንዲወስዱና ብቃታቸው እንዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡

በመሆኑም ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ የሚሆነውን አጠቃላይ ምዘና ወሰደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ስለዚህም ተማሪዎች ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተቋሙ ያሳስባል።

images: 
Share