News page

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀድሞ ምሩቃኑ ወርሃዊ የምክክር መድረክ ላይ ተገኘ
 
[ታህሳስ 01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
============================
በፖሊ ቴክኒክ ምሩቃን ተጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊ ካፌ ሲካሄድ የቆየው ወርሃዊ የመሰባሰቢያ መርሃግብር በዛሬው እለትም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት በዓል አከባበር የፖሊ ፔዳ ምሩቃን ተሳትፎ ኮሚቴ አማካኝነት በብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተካሂዷል:: 
መርሃ ግብሩ በያዝነው ዓመት እየተከበረ በሚገኘው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት በዓል አከባበር የቀድሞ ምሩቃንን ሚና መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በሰብሳቢው ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው አማካኝነት ተመርቷል::
አለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ቴክኖሎጂ እንስቲትዩት ተከበረ።
 
[ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ኢስኮ/ባቴኢ]
*************************************
በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ19ኛ በሐገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ዓለማቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስናን መታገል በተግባር!” በሚል መሪ ቃል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተከበረ።
መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት እንደተናገሩት፣ ሙስና የሀገር እድገትን በማደናቀፍ እና ህዝባዊ ስብዕና  መላሸቅ በማስከተል የሥራን ሞራል በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ስልሆነ በጋራ ልንታገለው ይገባል። በንግግራቸው አክለውም የሙስና መገለጫዎች ዘርፈ ብዙህ በመሆናቸው ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት፣ ባጋራ መስራት፣ መተባበርና በአንድነት በመቆም ሙስናን በእጅጉ መቀነስ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
The startup of BiTec, Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University, was named the best startup at the Entrepreneurship Competition held on the 9th Global Entrepreneurship Week, hosted by Ministry of Labor and Skills, Addis Ababa.
 
[December 04, 2022 Addis Ababa, ISC/BiT]
*************************************** 
The team of Solomon Geremew, Henok Simachew, Kalkidan Eshete, and Mequanint Ayusew BiTec-BiT-BDU, who pitched their business idea on the Ethio Organic Pesticide at the Entrepreneurship Competition on the Global Entrepreneurship celebrated in our country for the 9th time, was named the best startup and awarded 260,000 birr among the startups participated from various universities in Ethiopia. 

Pages