የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአልማዝ ኦዮቤልዩ በዓል

ለአንድ አመት ሲካሄድ የቆየዉ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአልማዝ ኦዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሄደ
[ሰኔ 04/2015 ዓ.ም፣ ባህር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ]
********************************
በጠዋቱ መርሃግብር የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት በዓልን በማስመልከት የቀድሞ ተማሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች የተሳተፉበት ታላቅ የጥበብ ሩጫ ተካሂዷል። ፕሮግራሙን የሚያደምቁ ልዩ ልዩ ትርኢቶች የተከናወኑ ሲሆን ዶ/ር ዘዉዱ እምሩ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በዓሉ አጋር አካላትን በመልካም ገጽታ ሲያስተሳስር እና ዓመቱን ሙሉ በደማቅ ሁኔታ ሲዘከር የቆየ እንደሆነ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ በንግግራችው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ዩኒየን በተጓዙበት ቀን የተጀመረው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምስረታ ጉዞ ለዛሬዉ ታሪካዊ ዕለት አድርሶናል ብለዋል። በንግግራቸውም ባለፉት 2 ዓመታት ለሰራተኞች እንዲሁም ለተማሪዎች ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር በአረንጓዴ አሻራ እያከናወነ ያለዉ ተግባር አስደሳች መሆኑ እና ቀጣይነት ሊኖረዉ እንደሚገባ ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አደም ፋራህ በበኩላችው በ60ኛ ዓመቱ የተገኘዉ መነቃቃት መቀጠል እንዳለበት ጠቁመው የተቋሙ የቀድሞ ምሩቃን ዩኒቨርሲቲዉን በሚችሉት መንገድ መደገፋቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። በመቀጠልም የዜማዉ ንጉስ አበበ ብርሃኔ ድንቅ ሙዚቃዊ መነባንብ አቅርቧል።በዕለቱ ትልቅ እና ልዩ የዕዉቅና እና ሽልማት ሥነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ራዕዩን እና ተልዕኮውን ለማሳካት በሚያደርጋችዉ አህጉራዊ እና ሃገር በቀል ግንኙነቶች ጉልህ ሚና ያላችዉ ተቋማት፣ኢምባሲዎች እንዲሁም በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ ሰራተኞች እና መምህራን እዉቅና ተሰጥቷችዋል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ፌስቡክ፡- Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et
Share