Events page

በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ2013ዓ.ም በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ ፈተናውን ላለፋችሁ በሙሉ በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በሚሰጡ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በ2013ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም ለመማር አመልክታችሁ የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ አመልካቾች የምዝገባና የትምህርት መጀመሪያ መርሃ-ግብር እንደሚከተለው መሆኑን እየገለፅን ተመዝጋቢዎች ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድና አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችን ኦሪጅናል እና ኮፒ ይዛችሁ በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባ እንድታካሂዱ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡  የምዝገባ ቀናት ህዳር 09—10 /2013 ዓ/ም በቅጣት 11/2013 ዓ/ም ነው፡፡

 ትምህርት የሚጀምርበት ቀን ህዳር 14/2013 ዓ/ም

 የትምህርት ማስረጃዎችን ኦሪጅናል እና ኮፒ

 ለ Application የከፈላችሁትን ኦርጅናል ድረሰኝ፡

 ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ(3*4)የሆነ፡፡

 የስፖንስር ሽፕ ድብዳቤ ዋናውን(ስፖንስር ላላችሁ)፡፡

 እስካሁን ድረሰ ኦፊሻል ትራንስክርቢት ያላስላካችሁ /ያልደረሰላችሁ እስከ ምዝገባው ቀን ድረስ እንዲደርስ አድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

(ትምህርታችሁን ለመቀጠል ያለፋችሁ አመልካቾች ስም ዝርዝር ከዚህ ማስታዎቂያ ገጽ የተቀመጠዉን ተጨማሪ መረጃ /attachment/ መመልከት ይቻላል፡፡

 

ባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲቱዩት

ሬጅስትራርና አሉሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ጽ/ቤት- ባህር ዳር

11 Nov 2020
BiT-Bahir Dar University

***********************************************************

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ2013 ዓ.ም በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትም/ት መስኮች ከአሁን በፊት በዊክንድ መርሃ ግብር (Weekend Program) ስናስተናግድ የነበረውን በ”Online” ፕሮግራም የስልጠና መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ በአዲስ አበባ ለማስተማር እስከ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ድረስ ማስታወዊያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የአመልካቾችን ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት የምዝገባ ጊዜውን እስከ ህዳር 20/2013 ዓ. ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዝሩትን ማስረጃዎች በ bitdistance@gmail.com ሞልታችሁ ከተቀመጠው የምዝገባ መጨረሻ ቀን በፊት ሞልታችሁ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 1ኛ. የመመዝገቢያ ቅጽ (Application form) 2ኛ. የባንክ ክፍያ ደረሰኝ (Bank Payment sleep) እንዲሁም “official transcript” በሚከተለው አድራሻ እንድትልኩ እናሳስባለን።
ባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ 
ፓ.ሳ.ቁ. 26 
ባህር ዳር 
ኢትዮጵያ
በተጨማሪም ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተመዝግባችሁ ክፍያ የከፈላችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ bitdistance@gmail.com የከፈላችሁበትን የከፍያ ደረሰኝ በማማያዝ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
9 Nov 2020
BiT-Bahir Dar University

Please get the attachment to check your name is from the list

31 Oct 2020
BiT,Bahir Dar University
21 Oct 2020
BiT-Bahir Dar University

Three imporatant attached files are downloadable to use for registartion

1. Weekend Program lists (Choose programs to your preference and based on your backgraound)

2. Application Form (Properly fill all empity required fields on applicaton list)

3. Forwarding Contact addresses. (Return back with the filled application form and other required documents)

9 Aug 2022
BiT-Bahir Dar University

በ2013 ዓ/ም የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ለመሆን ለሚፈልጉ አመልካቾች

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር በሚሰጡ የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በሚኖሩት ክፍት ቦታዎች የነፃ ትምህርት እድል ለመስጠት አቅዷል፡፡ እድሉን ላገኙ እጩዎች ዩኒቨርስቲው የትምህርት ወጭዉን ብቻ (የምርምር፣ የምግብ፣ የዶርምና የህክምና አገልግሎት ወጭን ሳይጨምር) የሚሸፍን መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ) በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት (እስከ መስከረም 30 ቀን 2013) የማመልከቻ ፎርማሊቲዎችን አሟልቶ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፤

ለ) በምዝገባ ወቅት ኢፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ለሬጅስትራር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

ሐ) የመጀመሪያ ድግሪ አማካይ ውጤት ለወንዶች 3.50፣ለሴቶች፣ለአካል ጉዳተኞችና የታዳጊ ክልል አመልካቾች 3.00 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፤

መ) የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ መሆን ይኖርበቸዋል፤

ሠ) ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ አጥ ማስረጃ፤

ረ) የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት ማመልከትና ለነፃ ትምህርት የተዘጋጀውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል::

ማስታዎሻ፦ የማመልከቻ ቅጹ፣ ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዟል

 

20 Sep 2020
BiT- Bahir Dar University

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2013 የትምህርት ዘመን አዲስ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎችን በመደበኛ መርሃ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ https://bit.bdu.edu.et/node/592 የማመልከቻ ቅጹን በማውረድና (Download) በመሙላት ትምህርቱ ወደሚሰጥባቸው የትምህርት ክፍሎች ሬጅስትራር E-mail አድራሻ በመላክ እንድታመለክቱ እያሳሰብን፡ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ትምህርቱ የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ሬጅስትራሮችን E-mail አድራሻ ከድረ ገጻችን እንድትመለከቱ እያስታወቅን ወቅታዊውን የጤና ችግር በማስታወስ ለሁላችንም ጤና ሲባል በአካል የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን!!!

ማስታዎሻ የማመልከቻ ቅጹ፣የትምህርት ክፍሎች ሬጅስትራር አድራሻ፣የትምህርት መስኮች ሁሉም ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዘዋል

 

17 Sep 2020
BiT-Bahir Dar University

Pages